ትንሽ ስለ ቋንቋ መብት: የ’ማንነት’ ጥያቄና ዘመቻ/አብርሃ ደስታ/

Abraha picትንሽ ስለ ቋንቋ መብት: የ’ማንነት’ ጥያቄና ዘመቻ
“አብርሃ ደስታ ማንነቱ የሸጠ ነው” የሚል ዘመቻ መጀመሩ ሰማሁ።  ዘመቻው የተከፈተው “መቐለ ተብሎ በትግርኛ ወይም መቀሌ ተብሎ በአማርኛ ቢፃፍ ችግር አይፈጥርም። የመቐለ ስም አልተቀየረም። በሌላ ቋንቋ ከተፃፈ ግን የግድ የድምፅና የፊደል ለውጥ ሊኖር ይችላል፤ ሁሉም ቋንቋዎች አንድ ስላልሆኑ”  ብዬ ስለፃፍኩ ነበር። ዘመቻው የከፈቱት ሰዎች የተወሰኑ የህወሓት ካድሬዎች፣ የተወሰኑ ‘ገለልተኛ’  ሙሁራንና የግል ጋዜጠኞች ናቸው። ማንነታቸው ሳውቅ ደስ አለኝ። ስለ ተጀመረው ዘመቻም በጣም ደስ ብሎኛል። ለምን? የህወሓት ካድሬዎች አይፈረድባቸውም። ፖለቲካ ነውና። እንደምንም ብለው እኔ መፃፍ የማቆምበት አጋጣሚ ቢፈጠር ደስታቸው ነው።
arena structureየባድመን መሬት ለኤርትራ ሲሰጥ ምንም ያልተነፈሱ፣ ኤርትራ ለማስገንጠል የተሟገቱ፣ ዓሰብ የኤርትራ ነው ብለው የሀገራቸው ብሄራዊ ጥቅም አሳልፈው የሰጡ፣ ዜጎቻችን በሌሎች ሀገሮች ሲሰቃዩ የሐዘን አስተያየት ያልፃፉ፣ የባህር በር (ወደብ) ማጣታችን ያላሳዘናቸው በመርከብ ስም (አንድ ፊደል መቀየር) ምክንያት ይህን ያህል ፔቲሽን ለማሰባሰብ ሲሯራጡ አይደንቅም። ፖለቲካ ነውና። ስለዚህ የህወሓት ካድሬዎች በኔ ላይ ዘመቻ ቢከፍቱ አልጠላቸውም። ለፖለቲካ ብለው ስለሆነ የሚያደርጉት። እኔም ቢሆን እተባበራቸዋለሁ። (ለመተባበር ያህል ነው በኔ ላይ ዘመቻ መጀመሩ በራሴ ፌስቡክ ገፅ ላይ በመፃፍ
የማስተዋውቀው)። የሙህራኑ ትችት ግን ይገርማል። ምክንያቱም ሰው ሲማር የባህሪይ ለውጥ ያመጣል ተብለን ተምረን ነበር። አንድን ቃል
በሌላ ቋንቋ ሲፃፍ የመጀመርያው (Original ) ትርጉሙ፣ ድምፁና አፃፃፉ (በቋንቋው ደንብ መሰረት) ሊቀየር እንደሚችል አለማወቃቸው ነው
የሚገርመው። የአንድን ህዝብ ወይ ከተማ ስም በሌላ ቋንቋ ተፅፎ የፊደል ለውጥ ስለመጣ ማንነቱ እንደተካ አድርጎ የሚያስብ ሙሁር መኖሩ
ሳውቅ አዘንኩ። የአንድን ህዝብ ማንነት በአንድ ፊደል ላይ የተንጠለጠለ አይደለም። ማንነት እንዳይቀየር (የቃል ትርጉም እንዳይለውጥ) በሌላ
ቋንቋ መፃፍ የለበትም አይባልም። ደግሞኮ ሙሁራኑ የሚፅፉት በእንግሊዝኛ መሆኑ ነው። በእንግሊዝኛ ቋንቋ መፃፋቸው በራሱ ችግር
የለውም። ራሳቸው በእንግሊዝኛ እየፃፉ ሌላ ሰው በአማርኛ ከፃፈ ማንነቱ አሳልፎ እንደሰጠ ተደርጎ ይሰበካል። ማንነታችን አሳልፈን
ላለመስጠት ከራሳችን (የአፍ መፍቻችን) ቋንቋ ዉጭ መፃፍና መናገር የለብንም ማለት ነው? ታድያ እነሱ ለምን በእግሊዝኛ ይፅፋሉ፣
ይማራሉ? ቋንቋ ፀጋ ነው። በራስህ ቋንቋ ብቻ ነው መፃፍ ያለብህ ያለው ማነው?  በምንችለው ቋንቋ ሁሉ መፃፍ አለብን። በእንግሊዝኛ ወይ
በአማርኛ ወይ በሌላ ቋንቋ መፃፍ ማንነት መለወጥ አይደለም። ይህን ያላወቀ ሙሁር አዝንበታለሁ። ሙሁር ማንነቱ መርሳት አለበት
አልተባለም። በእንግሊዝኛ ወይ በአማርኛ መፃፍ መቻል ግን ማንነትን መካድ አይደለም። ዘመቻው ከሚያጣጥፉ ግለሰቦች የተወሰኑ ደግሞ
ጋዜጠኞች መሆናቸው ነው። ታድያ ጋዜጠኞች መሆናቸው ምን ይገርማል? ጋዜጠኞቹ ራሳቸው የሚፅፉት በአማርኛ መሆኑ ነው። ራሳቸው
በአማርኛ እየፃፉ  “መርከባችን በአማርኛ ተፃፈች” ይላሉ። ዘመቻው ከሚያስተባብሩ ጋዜጠኞች አንዱ ራሱ በፃፈው የአማርኛ ፅሑፍ (በአንድ
የግል ጋዜጣ ላይ ነው። ‘የግል’ ያልኩት ለወግ ነው) ‘መቀሌ’ ብሎ ነው የሚፅፈው። አሁን ግን  “አብርሃ መቀሌ መባሉ ችግር የለውም አለ” ብሎ
አካኪ ዘራፍ እያለ ነው። ‘መቀሌ’ ተብሎ መፃፉ ስህተት መሆኑ ብታውቅ ለምን  ራስ ህ ‘መቀሌ’ እያልክ ትፅፈዋለህ? የማንነት ጉዳይ ነው
የሚባል  ነገር አለ። አዎ! ቋንቋ የማንነት ጉዳይ ነው። ቋንቋ የአንድ ህዝብ ማንነት፣ ባህል፣ ሃይማኖት፣ ታሪክ ወዘተ የሚፃፍበት (የሚገለፅበት)
መሳርያ ነው። ማንም ህዝብ የራሱ ማንነት የመጠበቅ፣ የፈለገው ሃይማኖት የመከተል፣ በመረጠው ቋንቋ የመፃፍ መብት አለው። ይህ መብቱ
ሊከበርለት ይገባል። መብቱ ሲከበርለት ግዴታውም መወጣት አለበት። መብትና ግዴታ አይነጣጠሉም። አንድ ህዝብ በመረጠው ቋንቋ
የመጠቀም መብት ወይ ነፃነት አለው። በቋንቋ የመጠቀም ነፃነት ማለት ያለ ሌሎች ህዝቦች ወይ ቋንቋዎች ተፅዕኖ (ጫና) በመረጠው (በራሱ)
ፊደል፣ ድምፅ፣ ስዋስው፣ ዘዬ ወዘተ የመፃፍ መብት ማለት ነው። ሌላ አካል መጥቶ የራሱ ቋንቋ፣ ፊደል ወይ ድምፅ ያለፍላጎትህ ሊጭንህ
አይችልም ማለት ነው። ማንኛውም ቋንቋ ለራሱ ጎደሎ አይደለም። ቋንቋ በራሱ ሙሉ ነው። ስለዚህ ማንኛውም ህዝብ በራሱ የመፃፍ መብት
ወይ ነፃነት አለው። አንድን ህዝብን ያለ ሌላ ህዝብ (ቋንቋ) ተፅዕኖ በመረጠው ቋንቋ የመጠቀም መብት ካለው ያ ህዝብ የሌሎች ህዝቦች
(ቋንቋዎች) መብት (ነፃነት) የማክበር ግዴታም አለበት። የትግራይ ሰዎች በራሳችን ቋንቋ ያለ ምንም የሌላ አካል ጫና በቋንቋችን የመጠቀም
መብት ካለን የሌሎች ህዝቦች መብትም የማክበር ግዴታ አለብን። ለምሳሌ እኛ በትግርኛ ‘መቐለ’ ብለን የመፃፍ ወይ የመናገር መብት አለን።
አማርኛ ተናጋሪዎች መጥተው ‘መቐለ ትክክል ስላልሆነ  መቀሌ በሉት’ ሊሉን አይችሉም። “አምሓርኛ  ትክክል ስላልሆነ  ‘አማርኛ’ ብላችሁ
በአማርኛ ፃፉት ብለው ሊያስገድዱን አይችሉም። አንድን ቃል በትግርኛ እንዴት እንደሚፃፍ የአማራ ወይ የአሜሪካ ሰው ሊያስተምረን
አይችልም (የትግርኛ ቋንቋ እስካላወቀ ድረስ)። ስለዚህ የትግራይ ሰዎች በፈለጉት ፊደል የመፃፍ መብት አላቸው። በተመሳሳይ መልኩ የትግራይ
ሰዎችም በሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎች ላይ ጫና በመፍጠር የሌሎች ህዝቦች በራስ ቋንቋ የመጠቀም መብት ሊዳፈሩ አይገባም። የየትኛው ሀገር
(ቋንቋ) ቃል በራስህ ቋንቋ የመፃፍ መብት አለህ። አማርኛ ተናጋሪዎች እንዴት የከተማ ስም ወይ ሌላ ቃል መፃፍ እንዳለባቸው የሚያውቁት
እነሱ ራሳቸው ናቸው። የትግራይ ሰው ወይ የአሜሪካ ሰው በአማርኛ ቋንቋ ላይ ጣልቃ ገብቶ እንዴት መፃፍ እንዳለባቸው ሊያስተምራቸው
አይችልም። የትግራይ ሰው ይህን ፊደል ወይ ድምፅ ወይ አክሰንት ተጠቀሙ ብሎ ማስገደድ አይችልም። ስሜ (በትግርኛ) ይሄ ነው ብሎ መናገር
ይችላል። “ስሜ ትግርኛ ስለሆነ እናንተም በአማርኛ ዉስጥ በትግርኛ ፃፉት፤ ፊደል ከጎደለባቹ ከኔ ዉስዱ” ብሎ ማዘዝ አይችልም። ሁሉም
ቋንቋዎ የየራሳቸው ፊደላት አሏቸውና። አንድ የትግራይ ሰው ለአሜሪካኖች የራሱ ፊደል ሰጥቶ የእንግሊዝኛው ስፔሊንግ ማስተካከል (መቀየር)
አይችልም። ለምሳሌ እኛ “ዓድዋ” እንላለን። አማርኛ ተናጋሪዎች “አድዋ” ብለው ቢፅፉት የግድ ‘ዓድዋ’ ብላች ሁ ካልተናገራቹ ወይ ካልፃፋቹ
ብለን ማለት የለብንም። በአማርኛ ቋንቋ እንዴት መፃፍ እንዳለባቸው የሚያውቁ እነሱ የቋንቋው ተጠቃሚዎች ናቸው። በእንግሊዝኛ ደግሞ
“Adwa” ብለው ቢፅፉት  “Adwa” ትክክል አይደለም “A” በ  “ዓ” መስተካከል አለበት አንላቸውም። ምክንያቱም እንግሊዛውያኑ  “ዓ”
ፊደል ይሁን ድምፅ የለንም ይሉናል። “‘ዓ’ ከሌላቹ ከኛ (ከትግርኛ) ተበደሩና  “ዓdwa” ብላቹ ፃፉ ብለን የእንግሊዝኛውን ስፔሊንግ የማበላሸት
መብት የለንም። በራሳችን ቋንቋ “መቐለ” ብለን እንዳንፅፍ የከለከለን አካል የለም፤ ካለም አንቀበለውም። በሌላ ቋንቋ ጣልቃ ገብተን እንዴት
እንደሚፃፍ ልንነግራቸው ግን አንችልም። ምክንያቱም የሌሎች በቋንቋ የመጠቀም መብት የማክበር ግዴታ አለብን። ማንነት ደግሞ ከራስ ጋር
የሚገናኝ እንጂ ከሌሎች ቋንቋዎች ጋር አይደለም። ብቻ በዚሁ ጉዳይ ብዙ ይቀረናል። አርእስቱም እንኳን ተነሳ። ብዙዎቻችን የግንዛቤ ችግር
እንዳለብን አልተገነዘብኩም ነበር። በዓለም ላይ ብዙ ቋንቋዎች አሉ። የራሳቸው ደንብም አላቸው። የራስ መብት ሲጠየቅ የራስ ግዴታ
መወጣትም ይጠበቃል። It is so!!!

ከኣዘጋጁ፡ ፅሑፉ ከፌስቡክ የተወሰደ ሲሆን ቀጥሎ እንደምትመለከቱት የድጋፍም የተቃውሞም ኣስተያየቶች ቀርበዋል፣ ፀያፍ ቃላት
የተጠቀሙትን በማስወገድ ሰዎቹ በርእሱ ያላቸው ኣቁዋም እንዳለ በማቅረብ ሌሎች ኣስተያየት እንዲያቀርቡበት እንደሚከተው ቀርቧል፡፡
  • Feyissa Gata Abrish in your argument , as you push to far right to win the argument, you seem to leave a big hole to the left. Who are these Amharic speakers who have the right to distort other languages in the country to suit them? Are you refering to Amhara? If so, then you will have an explanation as to why we should bother to please Amharic speaking nation. We need our language so that we freely use ours without bothering whether we have broken it or not.   I thought Amharic as a national language meant to accomodate all the nations and nationality accent slang and what have you up until your argument defending Amharic speaking ‘nation’.  Ah what a man?
  • Yaselam Yaselam Jezia good explanation for abraha  desta!
  • Akalu Nega well said Abrham, people outside of Tgiray have hard time to differentiate TPLF and People of Tgiray ,. that was good issue to talk about than this. as you well said it , it is our right to write it in way that the grammar or spelling laws of that particular language allows us. why people made it a big deal? I suspect TPlf try to change the subject to something they want.
  • Keshi Gebru yes it is akalu
  • Base Fano

  Andualem Bezabih Every thing is understood enough. please stop the dialogue on this weightless topic. I assured you that Tigrian-Ethiopians do have no problem with such use less agenda. It is the new fashion to spreed new hatred among peoples, collecting petition for silly  reason or untruth lectures. please therefore stop it to save your effort to the proper problem of your people.
 • Bantegizie Ambaw አበርሽ በርታ ሀሳብ ሲያጥርባቸው ሰድብ የረዝምባቸዋል የእኛ ሀገር ሰውች ……ፍጻሜኅን ያሳምርልህ እነደነ ጅዋር ሙሀመድ ኢትዮጵያን እንዳትከዳት
 • Berhe Alem :ልዋ ልዋ ተበሉዋስ ከምዚብሃል……………
  እዚ ወዲ ብድልየት ድጋፍ ናይ እኒ መስፍን ወልደማርያም ተመስገን ደሳለኝ ግርማ ሰይፉ ግዛቸው ሽፈራው ዝተለኸፈ ይመስል
 • Adex Weldegiorgis I found it interesting how Ethiopian government and its supporters are worried about people’s  culture and language while turning blind eye on People’s Poverty and injustice (in fact while covering it up or worse causing it)
 • Haben Asgedom , Abreha Desta. Do not you know that your boss Gebru Asrat is the one who give Aseb to Eritrea? Aseb is Ethiopia’s Port despite your boss’s decision. When you are bitterly defeated, you always start to go back to talk about irrelevant issues. When you feel good you try to tell us to forget the past and think the ….
 • Mesfin Mulugeta አማራ ክልል ብዙ ከተሞች በኦሮምኛ ስም ይጠራሉ ለምሳሌ ኮምቦልቻ፣ መርሳ፤ ውርጌሣ፣ ወልዲያ፣ ቆቦ…. ወዘተ በእነዚህ ቦታ የሚኖረው አማራ ነው እንደ ጠባቦች አስተሳሰብ ከሆነ ይህ ህዝበ የሚኖርበት ቦታ በቋንቋው ስለማይጠራ ማንነቱ ተነክቶል፡፡ ይህ ጉዳይ ግን አንድም ውቅት ለውውይት ጉዳይ ተደርጎ ቀርቦ አያውቅም መቅረብም የለበትም በቃ ስም መጠሪያ ነው ሰዎች በለመዱት ሲጠሩት ኑረዋል ይቀጥላሉ ሰ…
 • Ayalew Kerie Gebremeskel Well done Abrish!!! keep writing!! Never give up!!!
 • Hailu Bekele ልክ ነህ ‘መምህር’ አብራሃ ሰው ሲማር የባህሪ ለውጥ ካላመጣ መማሩ ትርጉም የለውም ሰርቴክፌት ስለያዘ ብቻ እንዳንተው ሁሉም አቃለሁ ካለና የሌሎቹን ሃሳብ ማክበር ካልቻለ ካልተማርነው ምን ለየው ? ለዚህ ነው አኔ ብቻ ነኝ አዋቂ አትበል አላዋቂነትህን ያሳብቅብሃልና ማለቴ። ይህ ካልኵኝ ዘንዳ ወደ ዋናው ጉዳዮ ልመለስ  ኤርትራ ማን ነው ያሰገነጠላው? ይህ ሃሳብ ስትገልፅ የሆነ ነገር አስታወስከኝ
  Biniyam Yeheyes pls abrish say samting abt machew hospital, we r proud of u!
 • Daniel Mandefro አብርሽ – እንደወትሮው ከማንበቤ በፊት Like አደረኩና ማንበቤን ቀጠልኩ የማንበብ ፋላጎቴ እየጨመረ መረዳቴ እየሰፋ ፅሁፍህን አንብቤ ጨረስኩ ። በስተመጨረሻ ግን አንደ ነገር ተረዳሁ አውቄአለሁ ብሎ ከደመደመ ለማወቅ ካለተዘጋጀ ጋር መነጋገርና እውቀትን share ለማድረግ መሞከርን የመሰለ አድካሚ እና ከባድ ነገር የለም አወንግዲህ ምን እልሀለሁ ወዳጄ ገብተህበታል  እግዚአብሄር ፀጋውን ያብዛልህ በርታ ።
 • Aden Ethiopia አታ እዚ ሰብኣይ ዓቢዱ ክመላልአና ደልዩ ! ኦ ንጎደፋይ ኦ ንጎደፋ ኦ ንጎደፋ ሃቢርና ንቅበሮ ! ዝብል ደርፊ ትዝ ኢሉኒ ፡፡
 • Sendekie Endawkie I cant name the word Mekele as the Tigray people,so what shall I do ? I have two alternative 1,naming in amharic accent As Mekela 2,totally stop naming the city Mekela.
 • Kibrom Wolday Tigrigna !!! ቋንቋችን ትግርኛ እንጂ ኣማርኛ ኣይደለም !
Kibrom Wolday's photo.
 • Aemro Yibeltal “እሳት አመድ ወለደ!”  ወጣት ስለመልካም አስተዳደር፤ ስለ ዉሀ እጦት፤ ስለ ዉጭ ጠላት እና የመሳሰሉትን አንስቶ ይወያያል እናንተ አንድ ፊደል ተቀየረ ብላችሁ አካኪ ዘራፍ ትላላችሁ፤ Any way all u r “ድንጋይ ራስ”
 • Aemro Yibeltal @Kibrom woldy እንደዚህ ብለል በምንኛ  እንደፃፍክ አዉቀሀል? Whether u like or not  u was ,is , will  use amharic language!
 • Kefyalew Habte አሁን ገና አብርሃ ደስታን ፈራሁት ለኢትዮጵያ ያለውን ትልቁን ምልከታውን ሁሉም ዜጋ እኩል የሚታይበትን ሥርዓት የመገንባት እልሙን መቀሌ መቐለ በሚል ተልካሻ ጉዳይ እንዳያሰናክል። እኔ ከአብርሃ የምጠብቀው፦
  ፩ አረናን ከሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር አዋህዶ ገዥውን ፓርቲ ሊገዳደር የሚችል አንድ ጠንካራ ፓርቲ መመሥረት
  ፪ አረናን ከክልል ወደ አገር አቀፍ ፓርቲነት መቀየር የመሳሰሉትን ታላላቅ ቁምነገሮችን ነው።
 • Hailu Bekele Daniel Mandefro እኔ ሃይሉ በቀለ ነኝ lol. ሰውን ሳይሆን አብርሃ ነው፤ ዘለፋ ሳይሆን በሚገባው ቋንቋ ነወ የነገርኵት። ዳንኤል ማንደፍሮ አንድ አባባል አለ ጅል ጀዝባ  ሲሉት ጀ ብቻ ወስዶ  ጅግና የሆነ መሰለው ነወ እና ነገሩ  ጅሉ ነገሮቹ በተሳሳተ መንገድ እንዳይገነዘበው ቢያጠፋም ባያጠፈም በቀን ሁለቴ ሊኮረኮምና ሊመከር ይገባል መቸስ አብርሃስ ወገናችን አይደል ዳሩ ፀበል የሚወሰደው…
 • Abebe Ayel #abrhaesta tenshu Dawet Talaqun Saole neqenqewu!!!!!!!!!
 • Abreham Simon abraha desta yagegnehewen hulu kadre bleh chereskew eko kkkkkkkkkk wey gud
 • Haile Siyum አብራሃ ደስታ ዝፅሕፎም ፅሕፋት አብ እዋን መረፃ ንህዝቢ ትግራይ እተተበቲኖም አረና ፓርቲ  ካብ ፖለቲካ ዎፃኢ ይገብሮ። ምክንያቱ መራፂ ህዝቢ ‘መቀሌ’  ዘይኮነስ ህዝቢ መቐለ ; ህዝቢ ትግራይ ጥራሕ ስለ ዝኮነ!! Thus TPLF will gain political advantage and Arena  Party will be out of the political game. Tamagne Beyene, Abebe Gelaw and Mesfin W/mariam will never come and give  a single vote in Mekelle. No space for them in Tigray, that means for you.
 • Mehari Berhane ኣብርሃ አማረኛ ምፅሓፍካ ኣይኮነን ፀገሙ ብጣዕሚ ዘሕዝን ግን ነቲ ይውክሎ እየ እትብሎ ህዝቢ ትግራይ ቁንቁ መንነቱን ዘይምፍላጥካ እዮ፡፡
  ንኣብነት. ኣብርሃ ብትግርኛ
          አብርሃ ብአማረኛ እንታይ ትርጉም ይህበካ?
 • Atikilt Honne መርከቧ ለትግራይ ክልል መናገሻ ለሆነችው መቐለ መታሰቢያ ስለሆነ ስሙ በቋንቋው ተናጋሪ መፃፍ አለበት፡፡
  ከዛ ውጭ ግን ሌላው (ትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ያልሆነ) ለምን መቐለ አላልክም አይባልም፡፡
  ስለዚህ ፍትሐዊ እንሁን…
 • Dawit Gebreselassie i’m really disappointed with all what you repeatedly say of ur a number of “heroes” residense-tigray and all its humble people!!!!!
 • Hailu Bekele Daniel Mandefro  የጣልያን ሽንት ቤት ከማጠብ ባሻገር ቢያንስ የአንድ ኮሌጅ ሰም ለማወቅ ሰለበቃህ አደንቅሃለሁ ጊዜ ሳገኝም ልፈርምልህ እችላለሁ እንኳን ደስ ያለህ። አየህ ደረጃህ የጠበቅ ደንቆሮ ነህ አልያም የሰው አገር ሽንት ቤት ከምታፀዳ የዛገው አዕምሮህን አፅዳ አንዳልልህ እንዳንተው ልሆን ነው ስለዚህ ማለቱ ትቸው አለሁ ። ጓደኛህ ሲጀምረው እንዳንተ ነበር የሚያደርገው ከሱ አስተሳሳብ…
 • Nigusu Shewatatek Yalew ለአቶ ሐይሉ በቀለ ለመሆኑ የምትጠቀመዉ ቃላት የአንድ አስተያየት ሠጪ ሳይሆን የሆድ አደር ቃል ነዉ ሽፋን የመሠጣቸዉ አካሎች ሊታዘቡህ ሁሉ ይችላሉ ህሊናህን ሸጠህ ለሆድህ መገዛትህን ቃላትህ ይመሠክራሉ ሆድ አደር የዉሐ ላይ ኩበት ነዉ
 • Hargussat Abay ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ አይሁዳዉያን ወግ ልማድ እና ባህል አደገ አንተ እንደማን ወግ ልማድ ባህል አስተዳደግ እዳደክ ብትነግረን ጥሩ ነበር በየትም አለም ማንም ህዝብ በወጉ በልማዱ በቛንቛው የሚኮራ ዝም ብሎ ይመስለሃል የማንነት ጥያቄ ስለሆነ ነው የትግራይ ህዝብም እንደሱ ጭቆና ከመረራቸው ያገራችን ህዝቦች ጋራ በመሆን የከፈለው መቼም ቢሆን የማይረሳው በድል የታጀበ ጉዞ ጥያቄ ስለነበረው ነው ..
 • Daniel Techan እኔ እምሰራዉና የምለዉ ሁሉ ትክክል ነዉ ብለህ ነዉ የምታስበዉ መሰለኝ (ከተሳሳትኩኝ ታላቅ ይቅርታ ግን ሓሳብህ ሁሉ እንደዛ ነዉ የሚገልፀዉ)….. በጣም የሚገርመኝ ኣንዳድን ጊዜ ጥሩ እሚባለ ሓሳባ ይዘህ ትቀርባለክ በዛ ልክ (ሳይበልጥ ይቀራል ብለህ ነዉ) ደግሞ የሞተ ሊባል የሚችል ወሬ ይዘክ ትማጎታለህ…. ኣሁን መፃፍ እና መናገር እንዴት ብሎ ኣንድ እንዲሆን ነዉ የምትጠብቀዉ  ….ለምሳ…See More
 • Zerihun Belete የሚገርመዉ እኮ እራሱን እንደ ባጃጅ መቆለሉ ነዉ
 • Yohannes Tadele @Abreha desta markabu yatasayamaw ba tigray wana katama naw katabala ya tigregna matakame ya ged naw.
 • Abrham Elias Daniel Techane Tadia Teregagiteh lemin Atasiredam?,,Endaynesirih!!haha
 • Tsegaye Seyoum abreshee ytwldkwe tgraye bhonme zgnethe ethiopian nwkoo …asredachwe mrkto ytwlede mrkatoiwi…wyme sfaa ldergwena addise ababa ytwlde adsbawiiiiiiiiiiiiiii….gudnw zndroo
 • Gerae Gerziher H ወይ ኣብረሃ ራስህን መቆለል እንደ ህፃን ልጅ ምን ፋይዳ አለው ብለህ ነው፤
 • Fesseha Akalu Dear Abraha, I share Daniel Techan’s concern. You’re increasingly becoming dismissive of other people’s opinion and labeling anyone, who even lightly and constructively criticizes you, as “cadre” and what not. Worse, it’s becoming blurred if you’re a f…See More
 • Teklit Guesh Shm bsru kkyer aykeln mekele  b tigrigna b amargna ewn mekele kkewn alewo tegaru amhargna enbl amhara sle zblu eu
 • Binyam Gebrewahid such a wonderful explanation!!!
 • Harnet Tesfay yetesheraref mannet ayasfelgenm bnls stet new?
 • Kefyalew Belay አብርሃ ችግሩ ያለማወቅ ሳይሆን እውቀትን ለተንኮል መጠቀም          (ሌላውን ጣልፎ ትርፍ ማግኛት ነው)
 • Wedi Mekelle abete aberha desta ande ken yegdeluhal weym be sebabe yaseruhal…any ways betame jagena tegraway eka…
 • አረጋዊ ለባም ሌባ ሌባ እንተበልዋስ ልዋልዋ ዝበልዋ ይመስላ መቀሌን መቐለን ከመይ ኢሉ እዩ ሓደ ዓይነት ትርጉም ሂቡካ
  ቅድሚ ሕጂ መቀሌ ሽሬ ኢልካ ስለዝፀሓፍካስ በቃ ንዘይምስትክካል ትማገት ዋይዋይ
 • Fetsum Berhane W http://danielberhane.com/…/ethiopia-gebrekidan-desta…/

  danielberhane.com

  (ዳንኤል ብርሃነ) እውቁ ደራሲና የታሪክ ተመራማሪ መምህር ገብረኪዳን ደስታ የኢትዮጲያ መርከብ ድርጅት አዲስ በተረከበው መርከብ… ላይ ‹‹መቀሌ›› ብሎ መፃፉ ስህተት መሆኑን ገለፁ፡፡ የኢትዮጲያ መርከብ ድርጅት ወደ ኢትዮጲያ የሚገቡና የሚወጡ ሸቀጦችን የማስናገድ አቅሙን ከ20% ወደ 50% ለማሳደግ በ2002 ዓ.ም…See More
Henock Ayalew As usual you have raised good/sound arguments Abraha Desta
 • Getachew Fantaye SEMERA is the capital city of Afar. Let us assume this name will be given to a ship. Can you write the name SEMERA. Remember Afar alphabet is known as Qafar Feera, the orthography is based on the Latin scrip. Now tell me how the name will be written on the ship understandable to all Ethiopians.
 • Bisrat Woldemichael All Aberha Deseta mentioned are absolutely correct! Hello Those who protest this idea! think rationalism, out from racism.Because globalization citizenship coming soon!
 • Keshi Gebru @Gech ezih bekirbu limelslih.Semera newa BE Federal yemitawekew sem esu selehone
 • Yihun O Tedla የህወሓት ካድሬዎች አይፈረድባቸውም።የባድመን መሬት ለኤርትራ ሲሰጥ ምንም ያልተነፈሱ፣ ኤርትራ ለማስገንጠል የተሟገቱ፣ ዓሰብ የኤርትራ ነው ብለው የሀገራቸው ብሄራዊ ጥቅም አሳልፈው የሰጡ፣ ዜጎቻችን በሌሎች ሀገሮች ሲሰቃዩ የሐዘን አስተያየት ያልፃፉ፣ የባህር በር (ወደብ) ማጣታችን ያላሳዘናቸው በመርከብ ስም (አንድ ፊደል መቀየር) ምክንያት ይህን ያህል ፔቲሽን ለማሰባሰብ ሲሯራጡ አይደንቅም????

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <strike> <strong>